ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደርቤ አስፋው ናቸው፡፡
ስምምነቱ በግሩፑ ስር በሚገኘው የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሚመረቱ የግብርና መሳሪያዎችን አርሶ አደሩና ማህበራት በብድር እንዲያገኙ ያስችላል፡፡
በግብርና ስራ የተሰማሩ ባለሃብቶች እና በማሽን ኪራይ የተሰማሩ በብድር አገልግሎቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ናቸው፡፡
በተጨማሪም ሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎቶችን፣ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትንና ለኢንዱስትሪው ሰራተኞች ብድር ማቅረብ የሚያስችሉ ስምምነቶች ተካተዋል፡፡
በስምምነቱ ወቅት የሁለቱ ተቋማት ሃላፊዎች በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡





