በሪፖርቱ የምርት፤ የፋይናንስ፤ የገበያ ልማትና አገልግሎት ማሻሻል፤ እንዲሁም የሰው ሃይል አቅም ግንባታ ሥራዎች በዝርዝር ቀርቧል፡፡
በዚህም ጥቅል የምርት አፈጻጸም 64.5% ማከናወን የተቻለ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት በ80% ዕድገት አሳይቷል ተብሏል ፡፡
የፋይናንስ አፈጻጸምን በተመለከተ የገቢ አፈጻጸም ከምርት እና አገልግሎት ሽያጭ 837.996 ሚሊየን ብር ለማግኘት ታቅዶ ክንውን 569,141 ሚሊየን ብር መፈጸሙና 68% መፈጸሙ ቀርቧል፡፡
ግብዓት ለማሟላት በበጀት ዓመቱ 186.14 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ታቅዶ ከግል ባንኮች ለ2 ኢንዱስትሪዎች 2.5 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ በማስፈቀድ ወደ ግብዓት ግዥ እንዲገባ ለማድረግ LC እንዲከፈት መደረጉ ተብራርቷል፡፡
የግሩፑ አጠቃላይ ገቢ(ሚሊየን ብር) 854 ሲሆን አምና ከተገኘው 461.65 ጋር ሲነጻጸር 139 ነጥብ 6 ወይም 30 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል፡፡
ትርፍ ከታክስ በፊት ዕቅድ 14.12 ሚሊየን ብር ታቅዶ 73.51 ሚሊየን ብር ተፈጽሟል፡፡
በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዳል፡፡
ግሩፑ ትርፋማነቱን ለማስቀጠል ያደረገው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ሲሆን ይህም ዘላቂ እንዲሆን አመራሩ ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት ቀርቧል፡፡የሁሉንም ኢንዱስትሪዎች ትርፋማነት ማረጋገጥ ይገባል ተብሏል፡፡
የጠራ የፋይናንስና የኦዲት ሪፖርት ወሳኝ በመሆኑ ስራው በፕሮጀክት ጽ/ቤት ደረጃ መጀመሩ የሚበረታታ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
የውጭ ምንዛሬ እና የብር ችግሮችን ለመፍታት በግሩፑ እየታዩ ያሉ አማራጮች ይጠናከሩ ተብሏል፡፡
አስተዳደራዊ ወጪዎችን መቀነስ፣ዘመናዊ ማሽኖችን በማሟላት ለላቀ ውጤት መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ በሆኑት በዶ/ር አብረሃም በላይ የተመራው ውይይቱ ከዚህ በተጨማሪ የውስጥ ኦዲት ሪፖርት፣የስጋት አስተዳደር ሪፖርትና ሌሎች አጀንዳዎችም ላይ ተወያይቷል፡፡




