ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከቻይና ከመጡ ኩባንያዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ።

ኢኢግ (25/02/2017 ዓ.ም)
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በቻይና ሃገር ቻንግሻ ከተማ ከሚገኙና የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ኩባንያዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
ኩባንያዎቹ በአውቶሞቲቭ፣በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ፣በግብርና ማሽነሪዎች፣ በሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት እንዲሁም በተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ሲሆን በቀጣይ ከግሩፑ ጋር ለመስራት የሚያስችላቸውን የትውውቅ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
ጤና ግዛው (ዶ/ር) የግሩፑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የምርምርና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ዘርፍ ሀላፊ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣቹ መልዕክት አስተላልፈው፤በቀጣይ በትብብር ለመስራት ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በእለቱም ስለ ግሩፑ አጠቃላይ ሁናቴና የሚያመርታቸውን ምርቶች በተመለከተ በግሩፑ የግብይትና የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ ታደሰ ጉርሙ ገለጻ የቀረበ ሲሆን በኮሚኒኬሽንና ፕሮሞሽን የተዘጋጀ አጭር ፕሮሞሽናል ቪዲዮም ለተሳታፊዎቹ ቀርቧል፡፡
በተመሳሳይ ከቻይና የመጡ የተለያዩ ኩባያንያ ባለቤቶችም ስለ ኢንዱስትሪያቸው ገለፃ አድርገዋል ።
ከሁለቱም ተቋማት በቀረቡ ገለፃዎች ላይም በአጠቃላይ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመስራት የሚችሉባቸው መንገዶች ላይ በቀጣይ ለመወያየት ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የውይይት መድረኩ በኢትዮጵያ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ማህበር አመቻችነት የተዘጋጀ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *