ጥቅምት 28 2017(ኢኢግ) በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የተሰሩ የምርምር ስራዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

በተለይም ሃገራችን ከውጭ የምታስገባቸውን መለዋወጫዎችና ልዩ ልዩ ግብአቶችን በሃገር ውስጥ እንዲመረቱ ለማስቻል በግሩፑ የተለያዩ የምርምር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ግሩፑ ኢትዮጵያ የራሷ ብራንድ ይገባታል በሚል መሪ ቃል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ የምርምርና ልማት ስራው ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎን ጨምሮ የቶፕ ሌቭል ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ውይይቱ ተካሂዷል፡፡
የግሩፑ ም/ል ዋና ስራ አስፈጻሚና የምርምርና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ዘርፍ ሃላፊ ጤና ግዛው (ዶ/ር ) እንዳሉት መድረኩ በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያዎች ያከናወኗቸው የምርምር ስራዎች ወደ ምርት የሚሸጋገሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነው፡፡
በመድረኩ ላይ አራት የምርምር ስራዎች ቀርበው ውይይት ተካሄዶባቸዋል፡፡
ዲዛይን የተጠናቀቀላቸውና በፕሮቶ ታይፕ ምርት ሂደትና በሙከራ ላይ ያሉት ዲስክ ፕሎው(ማረሻ )፣ትሬሼር ማሽን( የሰብል መውቂያ) የምርምር ስራ ቀርቧል፡፡
የዲዛይንና የአዋጭነት ጥናት የተሰራላቸውም ባለ 30 ኪሎ ዋት በጸሃይ ሃይል የሚሰራ ፓምፕ እና የፖሊመር ኮምፖዛይት ኢንሱሌተር የምርምር ስራዎች ቀርበዋል፡፡
በሌላ በኩል በግሩፑ 14 የምርምር ስራዎች እየተሰሩ የሚገኙ ሲሆን የስቲል መሸጋገሪያ ድልድይ፣ስማርት ሮታሪ ፓርኪንግ፣ የውድ ኬብል ድረም ማስ ፕሮዳክሽን ( ዲዛይንና ፕሮቶታይፕ የተሰራለት) ይገኙበታል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የግሩፑን የምርምር ስራ ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ የምርምር ስራ የሚሰራበት ወርክሾፕ ማመቻቸትና አስፈላጊውን ግብአት ማሟላት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
ኢንዱስትሪዎችም ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የተጠናከረ የምርምር ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *