አንድ መቶ N7 ፒክ አፕ ተሽከርካሪዎችን ያካተተውን የሽያጭ ሰነድ የኢትዮ ኢንጂሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፋፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና
የመንግስት ግዥ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ክፍሌ ገብረማርያም ተፈራርመዋል ።
የኢትዮ ኢንጂሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፋፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም በመጠቀም በቀጣይም የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ አየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክና አዋሽ ባንክ ለግሩፑ እና ለኢንዱስትሪው ላበረከቱት የፋይናንስ አቅርቦት ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም በጋራ በመስራት ኢንዱስትሪዎች ያላቸውን ምርት ተደራሽነት ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
የመንግስት ግዥ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ክፍሌ ገብረማርያም በበኩላቸው ከግሩፑ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት በማጠናከር በቀጣይም በሌሎችም ዘርፎች በጋራ መስራት እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹም ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለመንግሥት ተቋማት እንደሚከፋፈሉም አስታውሰዋል።
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክና የአዋሽ ባንክ ሀላፊዎችም የግሩፑን የፋይናንስ አቅም በመደገፍ አጋርነታቸው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን መንግስቱ ከኢንዱስትሩው ጎን በመሆን ለተሳተፉና ይህ ስራ ከግብ እንዲደርስ ለደገፉ አካላት ምስጋና አቅበዋል፡፡



















