የደንበኞች እርካታ ደረጃ የሚለይ ጥናት ማከናወን ጀመረ

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ደንበኞቹ ያላቸውን የእርካታ ደረጃ የሚለይ ጥናት ማከናወን ጀመረ፡፡
ግሩፑ ይህንን ጥናት የሚያከናውነው ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡
በሪፎርም ሂደት ውስጥ የሚገኘው ተቋማችን በቀጣይ የደንበኞችን እርካታ ለማረጋገጥ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከጥናቱ የሚገኘው ግብአትም ለዚሁ የሚሆን ነው፡፡
 
የጥናቱ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ሲካሄድ የተቋማችን ዋና ስራ አስፈጻሚና ፣የግብይትና ሽያጭ መምሪያ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የዩኒቨርስቲው ምሁራን በጋራ ምክክር አድርገዋል፡፡ ፈጣን ምላሽ መስጠት፤ የግዥ ትዕዛዝ አመላለስና የድሕረ-ሽያጭ አገልግሎት የደንበኛ እርካታ መለኪያዎች ዝርዝር ከቀረቡ አስር የጥናት ማመላከቻ ሐሳቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
 
ደንበኞች ስለተቋማችን ያላቸው ቅድመ-ግምት እና አገልግሎት ካገኙ በኋላ የ ድሕረ-ግምገማ በማጣመር ጥናቱ የሚካሔድ ሲሆን በሚቀጥሉት አራት ወራት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *