በግሩፑ ካይዘንን በመተግበር ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የሚያስችል አሰራር ለማስፈን ከኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ጋር በጋር እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ፕሮጀክት በፓወር ኢኪውፕመንት ማምረቻ ኢንዳስትሪና በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዳስትሪ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ፕሮጀክቱ የሚገኝበትን ደረጃ ሪፖርት አቅርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በሁለቱ ኢንዱስትሪዎች የካይዘን ትግበራው የደረሰበት ደረጃ የተገመገመ ሲሆን አሁን ከደረሰበት ደረጃ በላይ ፍጥነትን በመጨመር የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚገባው በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡ ተቋማቱ በካይዘን የተቀመጡትን አሰራሮች በመተግበር ምቹ የስራ ሁኔታን መፍጠር ላይ እንዲሁም ብክነትን በመቀነስ እና የምርት ጥራትን በማስጠበቅ ላይ ተከታታይ ስራዎችን መተግበር እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
የሚሰሩና የማይሰሩ ፣ጥቅም የሚሰጡና የሚወገዱ ንብረቶችን በአግባቡ በመለየት ወደ ፊት መጓዝ ይገባልም ተብሏል፡፡ ካይዘን አሁን እየተተገበረባቸው ከሚገኙት ከሁለቱ ኢንዳስትሪዎች በተጨማሪ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣በአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዳስትሪ፣በአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ኢንዳስትሪ፣በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዳስትሪ በሚጀመርበት ሁኔታ ላይም ውይይት ተካሂዷል፡፡
ከውይይቱ በተጓዳኝ የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስና የቢሾፍቱ አውቶሞቲበቭ ማምረቻ ኢንዳስትሪ ተጎብኝተዋል፡፡የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ህይወት ሞሲሳና የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እንዳወቅ አብቴ እንዲሁም ከካይዘን ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መኮንን ያኢና የተቋሙ ባለሙያዎች በጉብኝቱና በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡