ነሀሴ 6/ 2017 ዓ.ም (ኢኢግ) በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው ኢግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

በአየር ለውጥ ላይ ያተኮረው ለሁለት ቀናት በሚቆየው ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የኤሌክትሪክ ገመዶች፣ ሶላር ፓኔሎችንና በፀሀይ ሀይል የሚሰሩ መብራቶችን ለዕይታ አቅርቧል፡፡
ኤግዚቢሽኑን የከፈቱት የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢንጅነር ሱልጣን ወሊ ሲሆኑ  የአየር ንብረት ለውጥ የዘመናችን ችግር ነው ብለዋል፡፡ የኤግዚቢሽኑ ዓላማ የኢነርጂ አጠቃቀም ለውጥ በማምጣት የአየር ለውጥን መከላከል ይገባል ብለዋል፡፡
በታዳሽ ሀይል ላየ ትኩረቱን አድርገው የሚሰሩ ተቋማትና ለታዳሽ ሀይል የሚያገለግሉ ምርቶችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች የኤግዚቢሽኑ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *