የስራ አመራር ቦርዱ ከጉብኝቱ በተጨማሪ የተለያዩ ጉዳዮችም ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በጉብኝቱ በኢንዱስትሪው የሚገጣጠሙና የሚመረቱ የተለያዩ ትራክተሮች፣የማሽነሪ ተቀጽላዎች፣የውሃ ፓምፖች ፣ የመለዋወጫ ስቶሮች እና የማምረቻ ፋሲሊቲዎች ተጎብኝተዋል፡፡
የግሩፑ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አብረሃም በላይ(ዶ/ር) ኢንዱስትሪው ለሃገሪቱ የግብርና እድገት ያለውን ሚና ለማሳደግ በይበልጥ ዘመናዊ ለማድረግ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡
ዘመናዊ እና ወቅቱ የደረሰበት ቴክኖሎጂ ላይ ለመድረስ ጥረቶች መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ኢንዱስትሪው በርካታ ትርክተሮችን ለገበያ ለማውጣት የሚያስችለው ጉዳይ ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡
የስራ አመራር ቦርዱ የግሩፑን አሰራር ሊያሳድጉ የሚችሉ የተለያዩ አራት መመሪያዎችም ላይ ተወይይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ግሩፑ አጠቃላይ አሰራሩን ለማዘመን፣ተጠያቂነት ያለበትን አሰራር ለመዘርጋት የሚያስችሉ እና ከወቅቱ ጋር ተናባበቢ የሆኑ 15 መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ወደ ስራ በማስገባት ላይ ይገኛል፡፡



