ከኢትዩጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ወ/ሮ አስማ ረዲ ግሩፑ ከፍተኛ የሆነ አቅም እንዳለው ገልፀው፤ ለሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የግሩፑ ስራ አመራር ቦርድ አባል አቶ አየለ ከበደ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ግሩፑን የተሻለ ትርፋማ ለማድረግ ሁሉም ድርሻውን መወጣት እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ በበኩላቸው 2018 ዕቅድ ካለፉት አመታት እቅድ አፈፃፀም አንፃር ከፍተኛ እድገት ለማስመዝገብ የተያዙ ዕቅዶች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የበጀት አመቱን ዕቅድ ለማሳካት ከስራ አመራር ቦርድ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ምርምርና ኢኖቬሽን ላይ ትኩረት በማድገግ ሁሉም አመራርና ሰራተኛ ሚናውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ በተለያዩ ዘርፎች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ በግሩፑ ስር ለሚገኙት ሰባት ኢንዱስትሪዎች የዕውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ በፕግራሙ ላይ የግሩፑ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀምና የ2018 በጀት አመት እቅዶች ቀርበዋል፡፡
በመርሀ ላይ ከኢንዱስትሪና የዋናው መ/ቤት አመራርና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡






