እውቅና የተሰጠው በ2017 አ.ም በግሩፑ የስልጠና ማእከል ለሰለጠኑ 319 ባለሙያዎች ነው፡፡
ስልጠናው በምህንድስና፣ በምርታማነት፣ በአስተዳደር እና በቴክኖሎጂ ክህሎት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ስልጠናው የቲዎሪ እንዲሁም በኢንዱስትሪዎች የተግባር ልምምድን መሰረት ባደረገ መልኩ ተሰጥቷል፡፡
በዕውቅና መርሃ ግብሩ ላይ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ ግሩፑ በተለያዩ መስኮች እያደረገ ያለውን የለውጥ ስራዎች ለማፋጠን የሰልጣኞች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ግሩፑ ትላልቅ ሃገራዊ ተልእኮዎችን ለመፈጸም፣ፕላንት ዲዛይን ማድረግና ማምረትን ጨምሮ ኢንዱስትሪውን ለማስፋፋት መቋቋሙን በመግለጽ በዚህ ሂደት ውስጥ ሙያተኛው አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በመሆኑም ሰልጣኞች በፍጥነት ወደ ትግበራ መግባት እንዳለባቸውና ያገኙትን እውቀት ለሌሎች ለማስተላለፍ መትጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የግሩፑ ም/ል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የምርምና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ዘርፍ ሃላፊ አብዱልፈታህ ሼህቡሂ(ዶ/ር) በበኩላቸው ሰልጠናው ተቋሙን ለማሳደግ ያለውን ፋይዳ በመግለጽ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የስልጠና ፍላጎት በመለየት፣የስልጠና ሞጁል በማዘጋጀት እና ስልጠናውን በመስጠት ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ለሰልጣኞች፤ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሰልጣኞች፣ ለአሰልጣኞች እና ለግሪን ቴክ አፍሪካ የሰርተፊኬት እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡




