መስከረም 19/2018 አ.ም(ኢኢግ) ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና ኦሞ አዲስ አግሪፕላትፎርም በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ተቋማቱ በካሳቫ የግብርና ምርት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ነው የተፈራረሙት፡፡
በስምምነቱ መሰረት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በካሳቫ ምርት ለተሰማሩ እና ለሚሰማሩ አርሶ አደሮች እና ባለሃብቶች የግብርና ማሽነሪዎችን እና ለእርሻ መሬት ዝግጅት የሚያገለግሉ ማሽነሪዎችን ያቀርባል፡፡
ኦሞ አዲስ አግሪፕላትፎርም በካሳቫ ምርት አርሶ አደሮችን የማደራጀት፣ ካፒታል የማስተባበር እና ገበያ የማመቻቸት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ሁለቱ ተቋማት የካሳቫ የግብርና ምርትን ለማሳደግ እና የሃገሪቱን ግብርና ለማዘመን እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ የአርሶ አደሩን ህይወት ማሻሻል በስምምነቱ ተካቷል፡፡
የሃገሪቱን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥም የስምምነቱ አላማ ነው፡፡
በስምምነቱ ወቅት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ ስምምነቱ በቶፕ ማኔጅመንት ደረጃ እንደሚመራ አረጋግጠው የግብርና ማሽነሪዎችን ለማቅረብ ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡
የኦሞ አዲስ አግሪፕላትፎርም ም/ል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤርሲዶ ላንደቦ(ዶ/ር) የካሳቫ ምርት በሃገራችን በተወሰነ ደረጃ ለምግብነት እየዋለ እንደሆነ በመጥቀስ ይህንን ማስፋፋት እና ለውጭ ሀገር ገበያ ለማቅረብ እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴ ገልጸዋል፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ እና የኦሞ አዲስ አግሪፕላትፎርም ዋና ስራ አስፈጻሚ ካሳሁን አድማሱ ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *