ህዳር 30/2018ዓ/ም(ኢኢግ) የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኢንዱስትሪዎች የገበያ ድርሻ፣ የደንበኞች እርካታ እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ላይ የተደረገ ጥናት ቀረበ።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጥናቱ ቀርቧል።
በቀረበው ጥናት መሠረት የግሩፑ የደንበኛ እርካታ ደረጃ መሻሻል የታየበት ቢሆንም ከዚህም በላይ ማደግ እንዳለበት ተመላክቷል።
ጥናቱ ለቀጣይ ተቋማዊ ስራዎች መነሻ ሆኖ የሚያገለግል እና ምክረ ሃሳቦችንም ያካተተ ነው።
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ በተሰራው ጥናት መነሻነት በጥራትና በጊዜ ምርትና አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ሁሉም አመራርና ሰራተኛ ግሩፑ የተቋመበትን ራዕይ ለማሳት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
የግሩፑ ም/ል ዋና ስራ አስፈፃሚና የምርምርና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዘርፍ ሀላፊ አብዱልፈታህ ሼክ ቢሂ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢንዱስትሪዎች በሚያቀርቧቸው ምርትና በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን በጥናቱ ላይ የተመላከቱ ምክረ ሀሳቦችን ወደ ተግባር መቀየር እንደሚገባ ገልፀዋል።
በቀረበው ጥናት ላይ ለቀረቡ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የዩንቨርስቲው ተመራማሪዎች ማብራሪያ ሰጥተውበታል።
በተጨማሪም ተመራማሪዎች ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሊሰራ ስለሚገባቸው ጉዳዮችም ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል።
ለአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ጥናቱን ላጠኑ ተመራማሪዎች የዕውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ከግሩፑ ተበርክቶላቸዋል።
የግሩፑ ከፍተኛ አመራሮችና የዋናው መ/ቤትን ጨምሮ የኢንዱስትሪ አመራርና ሰራተኞች በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።











