ታህሳስ 1/2018 አ.ም (ኢኢግ) ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በመጀመሪያው የአፍሪካ የኢነርጂ ቁጠባ ኮንፈረንስና አውደርእይ ላይ እየተሳተፈ ነው።
በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ በሚገኘው መርሃ ግብር ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ ዓሊ የሱፍ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተገኝተዋል።
የአፍሪካ የሃይል ቁጠባ ላይ ባተኮረው በዚህ ጉባኤ ላይ ከኢትዮጵያ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አውቶማቲክ ፓወር ፋክተር ኮሬክተርና የሶላር ምርቶችን በአውደርዕዩ አቅርቧል።
የግሩፑ ም/ል ዋና አስፈሚዎች እና የማኔጅመንት አባላት በመርሃ ግብሩ እየተሳተፉ ይገኛሉ።











