የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ ኡመር እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ እና ከግሩፑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ግሩፑ ለክልሉ በሚያቀርበው ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን በተመለከ ተወያይተዋል፡፡
በተጨማሪም በግሩፑ ስር የሚገኘው አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በጅግጅጋ የሚገነባውን የድህረ ሽያጭ ማእከል አዲስ ዲዛይን አቅርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በዘመናዊ የግብርና ማሽነሪዎች አቅርቦት በጋራ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡








