የፀረ ጾታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን) ቀን እና የአለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ::

ህዳር 28/2014 የፀረ ጾታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን) ቀን እና የአለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ። የፀረ ጾታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን) ቀን በአገራችን ለ16ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ የተከበረው ይህ ቀን በኢትዮዽያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በፓናል ዉይይት እና አስተማሪ ፕሮግራሞች ተከብሯል ፡፡በእለቱም የኢንዱስትሪዉ ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።የፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀንን ስናከብር ሴቶችን በሁሉም ረገድ ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ የሰው ሀይል አስተዳደርና ልማት ሀላፊ አቶ ካሳ ተሾመ ናቸው። የሕብርተሰባችን ግማሹ ክፍል የሆኑት ሴቶችን በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖሎቲካዊ ተሳትፏቸውን በጨመሩ ቁጥር የሚያሳድሩት አውንታዊ ተጽኖ የላቀ በመሆኑ ይበልጥ ወደ ፊት እንዲመጡና መሪ ተዋናይ እንዲሆኑ ሊበርታቱ ይገባል።በግሩፑ አሰራሮችን ስርአተ ፆታ አካታች በማድረግ የሴቶችን ዉሳኔ ሰጪነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል።በዓሉ “ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም” በሚል መሪ ቃል ከህዳር 16 እስክ 30 በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበር ይገኛል። በተመሳሳይም የአለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን “በስነ ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በኢንዱስትሪው ተከብሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *