በዛሬው እለት በዋናው መ/ቤት ሀገር አቀፉ የፀረ -ሙስና ቀን ተከብሯል ።

ሙሰና የብሔራዊ ደህንነት ስጋት በመሆኑ በመከላከሉ ረገድ ሁሉም አካል የበኩሉን መወጣት እንደሚገባው የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናገሩ።
በዛሬው እለት በዋናው መ/ቤት ሀገር አቀፉ የፀረ -ሙስና ቀን ተከብሯል ።
የፀረ-ሙስና ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ 19ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ለ 18ኛ ጊዜ “ሙስናን መታገል በተግባር” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶችና በፓናል ውይይት ተከብሯል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተቋማችን ሰፊ የሆነ ሀብት የሚያንቀሳቅስ በመሆኑ የሙስና ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚያችል የአሰራር ስርአት ለመዘርጋት እየተከናወነ የሚገኘው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በተለይም ወደ ዲጂታይዜሽን በመግባት አሰራሩን ማዘመን እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ሙስና ሀገራዊ ነቀርሳ ነው ያሉት አምባሳደሩ ይህን ለመቅረፋ ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ አመላክተዋል።
በእለቱም በተካሄደው ውይይት ላይ የተቋሙ የስነ-ምግባር አገልግሎት ሀላፊ አቶ በላይ ለገሰ ስለ ጉዳዩ ገለፃ አድርገዋል።
በፕሮግራሙ ላይ አስተማሪ የቪዲዮ ቅንብሮችና የጥያቄና መልስ ወድድሮችም ቀርበዋል፡፡
ሙስና በሀገራችን ካሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ከኑሮ ውድነትና ከስራ አጥነት ቀጥሎ በሶስተኛ ደረጃ የሚገኝ ችግር በመሆኑ ይህን ለመቅረፍ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተመላክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *