በጉብኝቱ ወቅት በኢንዱስትሪው የስራ እንቅስቃሴ ላይ በኢንዱስትሪው አመራሮች ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
ኢንዱስትሪው በተለይም የፕላስቲክና የፖሊመር ምርቶች ላይ በማተኮር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ለቤትና ለቢሮ ግንባታ የሚውሉ የተለያዩ የኮምፖዛይት ምርቶችን፣ የተለያየ መጠን ያላቸው የፓይፕ እና የኮንዲውት ምርቶች፣ የቤት ወስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በደንበኛ ትእዛዝ የሚመረቱ የተለያዩ የፕላስቲክና የኮምፖዛይት ምርቶችን እያመረተ እንደሚገኝ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
በዚሁ ወቅት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እንዳሉት ኢንዱስትሪው በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ሚና የመጫወት አቅም ያለው ነው፡፡
የፓይፕ ምርቶቹ ለሃገራችን የመስኖ ስራ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም አስረድተዋል፡፡
የሃገሪቱን የውሃ ሃብት አሟጠን በመጠቀም ግብርናውን ለማዘመን የፓይፕ ምርቶቹን ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
መሰረታዊ የህዝብ ፍላጎት የሆኑ የፕላስቲክ ምርቶቹም ከከተማው ባሻገር ለገጠሩ ማህበረሰብ ተደራሽ እንዲሆኑ የማምረት አቅም ማደግ እንዳለበት ጠቅሰዋል፡፡
አምባሳደር ሱሌይማን አክለውም ኢንዱስትሪው በዘርፉ ላይ የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ግሩፑ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎችና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡21:21