ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በ “ኢንቨስት ኢትዮጵያ” አለም አቀፍ ፎረምና ኢግዚብሽን ላይ እየተሳፈ ነው፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በ “ኢንቨስት ኢትዮጵያ” አለም አቀፍ ፎረምና ኢግዚብሽን ላይ እየተሳፈ ነው፡፡
“ኢንቨስት ኢትዮጵያ” በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን አስተባባሪነት የሚዘጋጅና አለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የኢንቨስትመንት ፎረም እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣የክልል ፕሬዝዳንቶችና የአለም አቀፍ ኩባንያዎች ተወካዮች እየተሳፉ ይገኛሉ፡፡
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በኩልም የግሩፑን ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፣ የግሩፑ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎችና የኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጆች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ኮምሽነር ለሊሴ ነሜ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት እድሎችን አስተዋውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ግንባታና በኢትዮያ አየር መንገድ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶችና ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን አስተዋውቀዋል፡፡
የውጭ ኩባንያዎች መዋለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ፈጣን የኢንቨስትመንት አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ያለውን ስራ አብራርተዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን በግሉ ዘርፍ ለመደገፍ እያደረገች ያለቸውን እንቅስቃሴ፤በሃገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶችን ገልጸዋል፡፡
ፕሮግራሙ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር ለመስራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚደግፍ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *