ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በኢትዮጵያ ታምርት 2015 ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በኢትዮጵያ ታምርት 2015 ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡
በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘውን ኤክስፖውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከፍተውታል፡፡
የኤክስፖው አላማ አምራች ኢንዱስትሪዎች የርስ በርስ ትስስርን የሚፈጥሩበትን መንገድ ማመቻቸትና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተብራርቷል፡፡
ዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም ማስተዋወቅም የኤክስፖው አላማ ሲሆን የፓናል ውይይቶችም ምክክር ይደረጋል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕም በዘጠኙ ኢንዱስትሪዎች የሚመረቱ ምርቶችና ልዩ ልዩ ማስታወቂያዎችን በማቅረብ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚሁ ኤክስፖ ላይ ከ124 በላይ መከሰከለኛ እና ከፍተኛ አምራቾች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *