የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግሩፑ የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ የላቀ ሚና እንደተጫዋተ ተገለፀ።

የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግሩፑ የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ የላቀ ሚና እንደተጫዋተ ተገለፀ።
ነሐሴ 22/2015 ዓ.ም(አዳማ)
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ግሩፑ የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ የኢንዱስትሪው ሚና የላቀ ነው ብለዋል።
በዛሬው እለት ኢንዱስትሪው የ2015 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርት ላይ እንዲሁም የ2016 ዓ.ም እቅድ ላይ ተወያይቷል።
በእለቱም የቀጣይ በጀት አመት እቅድ በኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ታደሰ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጪው በጀት አመት ግሩፑ ከያዘው የሽያጭ እቅድ ሁለት ቢሊየን በላይ ከኢንዱስትሪው የሚጠበቅ መሆኑ ተመላክቷል።
አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ከአቅርቦት ማነስ፣ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ከዋጋ አለመረጋጋት ጋር ታግሎ የምርት ሂደቱን እንዲቀጥል ላስቻሉ ለኢንዱስትሪው ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ኢንዱስትሪ ማለት ሰው ነው፤የሰራተኛ እድገት ለሀገር እድገት መሠረት ነው ያሉት አምባሳደሩ ሀገራችን የምትከተለውን የግብርና ኢኮኖሚ ለማዘመን ተቋማችን እርሾ ሆኖ መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ ገልፀዋል።
በቀጣይም ከመገጣጠም ባለፈ ኢንዱስትሪው የራሱን ብራንድ አምርቶ ማሳየት አለበት፤ለዚህም የተጀመሩ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በሀላፊነት መተግበርና ከግብ ማድረስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተለያየ ፈረስ ጉልበት ያላቸውን ትራክተሮች፣የትራክተር ተቀፅላ ምርቶች፣የውሃ መርጫ ፓምፖችን በማምረት፣የጥገናና የድህረ ሽያጭ አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል።
በእለቱም በበጀት አመቱ ኢንዱስትሪው የተሻለ አፈፃፀም እንዲያበረክት አስተዋፅዎ ላበረከቱ ሰራተኞች፣ለስራ ክፍሎች እንዲሁም ድርሻ ላላቸው አካላት የዕውቅና ስጦታ ተበርክቷል።
በመርሃግብሩ ላይ የግሩፑና የኢንዱስትሪ ከፍተኛ አመራሮች፣የኢንዱስትሪው ሠራተኞች፣ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *