ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ 14 ኛው አዲስ ቻምበር አለም አቀፍ ንግድ ትርኢት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ 14 ኛው አዲስ ቻምበር አለም አቀፍ ንግድ ትርኢት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
የአዲሰ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው ይህ ኤግዚቢሽንና ባዛር በዛሬው እለት የመክፈቻ ስነ-ስርአት በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ አዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ኢትዮ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ፣ፖወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪና ኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ምርቶቻቸውን በኤግዚቢሽኑ ላይ አስተዋውቀዋል።
ከ 70 በላይ የሚሆኑ የሀገር ውስጥ አምራቾችና 15 የውጭ ሀገራት ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ነው።
ኤግዚቢሽኑ ሀገራችን ላይ ያሉትን አምራቾች በአንድ ቦታ በማገናኘት የልምድ፣የገበያ፣የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር እንዲያረጉ ይረዳቸዋል።
በተጨማሪም የከተማ ግብርና በማስፋፋት በሀገራችን የተጀመረውን የሌማት ቱሩፍት ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚረዳም ተገልጿል።
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሀገር ውስጥ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ከውጭ የመጡ እንግዶች ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *