ስምምነቱን የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የፋሬሲን ፎርምወርክ ኩባንያ ዋና ዳይሬክተር ጊያኮሞ ዳላ ፎንታና ተፈራርመዋል።
የተፈረመው የ3 ሚሊየን ዩሮ የኮንትራት ስምምነት በግሩፑ ስር የሚገኘውን የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምደው ነው፡፡
ስምምነቱ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአልሙኒየም ፎርም ዎርክን በሃገሪቱ በብቸኝነት አምራች የሚያደርገው ነው፡፡
በስምምነቱ መሰረት ፋሬሰን ኩባንያ ምርቱን ለማምረት የሚያስችሉ ማሽኖችን ፣ሲኬዲ እና ኤስ ኬዲ ምርቶችን ያቀርባል፡፡
የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የትብብር እና የማማከር ስራችም በስምምነቱ መሰረት የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ስምምነቱ ሃገሪቱ በዘርፉ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪም ያስቀራል፡፡
የአልሙኒየም ፎርም ዎርክ ቴክኖሎጂ ወደ ሃገራችን መግባቱ የግንባታው ዘርፍ እንዲዘምን ያደርገዋል፡፡
የሰው ሃይል ጉልበትን በመቀነስ፣ የግባንባታ ፍጥነትና ጥራት እንዲጨመር የሚያደርግ ነው፡፡
ፋሬሲን ፎርም ወርክ ኤስ.ፒ.ኤ በጣሊያን እና በመላው አለም የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች በማምረት ፣በመሸጥ የሚታወቅ የማኑፋክቸሪንግ ኩባንያ ነው።