የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የስቶር ካይዘን ትግበራ ማጠቃለያ እና የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የጥራት ስራ አመራር ስርዓት (QMS- ISO 9001:2015) ትግበራ ዕውቅና እና ሽልማት መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የስቶር ካይዘን ትግበራ ማጠቃለያ እና የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የጥራት ስራ አመራር ስርዓት (QMS- ISO 9001:2015) ትግበራ ዕውቅና እና ሽልማት መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የጥራት ስራ አመራር ስርዓት (QMS- ISO 9001:2015) ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የዕውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቶታል፡፡

በመርሃ- ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በመልዕክታቸው በኢንዱስትሪው ካይዘንን ለመተግበር በተሰራው ስራ በመጨረሻም ለውጤት መብቃቱ አንድ እርምጃ የሚያራምድ በመሆኑ የካይዘንን ፍልስፍና የኔ ነው ብለን ማስቀጠል እደሚገባ አሳስበዋል፤አክለውም ስርቆትንና ብክነትን በመዋጋት ሀብታችንን ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ማዋል ይኖርብናል ያሉት አምባሳደሩ መታወቂያችንን ጥራት በማድረግ ከውጪ እየመጡ የሚገጣጠሙ ማሽነሪዎችን በሀገር ውስጥ የማምረት ሂደት መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአዳማ ግብርና መሳሪያዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሽመልስ ጥላሁን ይህ ውጤት እንዲገኝ የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በቀጣይም በከፍተኛ ጥራትና ውጤታማነት ኢንዱስትሪውን ለማስቀጠል በይበልጥ መትጋት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ያከናወናቸውን የካይዘን ትግበራ የተጎበኘ ሲሆን ግሩፑ ከመስረም 1- ጥቅምት 30, 2017 ዓ/ም በዋናው መ/ቤትና በዘጠኙም ኢንዱስትሪዎች ላይ በፕሮጀክትነት ተይዞ ሲተገበር በነበረው የንብረት አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ ማጠቃለያ መርሀ ግብር ተካሂዷል።
በጉብኝቱ ወቅትም በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው የነዳጅ ማደያ በእለቱ ተምርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

የስቶር ካይዘንና ኮምፓውንድ ካይዘን ትግበራ ላይ በፈጠራ እና ማሻሻያ ስራ ላከናወኑ ፣በነበረው ትግበራ ላይ ለተሳተፉ አካላት እና አስተዋፅኦ ላበረከቱ ቡድን አባላት የምስጋና እና እውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከአንድ እሰከ ሶስት በመውጣት መልካም አፈፃፀም ላስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎች የዋንጫ እና የምስጋና እውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የግሩፑ የቦርድ አባል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዲንሰፋ መንሱር በቀጣይ ቀሪ ኢንዱስትሪዎችን ሰርቲፋይ የማድረግ ሂደቱን በቁርጠኝነት መተግበር እንደሚገባ ገለፀው፤ መልካም የስራ ጊዜ ተመኝተዋል።
በተያዘው በጀት አመት በግሩፑ ስር የሚገኙ ሁሉንም ኢንዱስትሪዎች ሰርተፍኬቱን እንዲያገኙ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይህም ግሩፑን የበለጠ አምራችና ተወዳዳሪ ያደርገዋል፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋ/መቤትን ጨምሮ ኢትዮጲያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ እና አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የጥራት ስራ አመራር ስርዓት (QMS- ISO 9001:2015) በመተግበር ዕውቅና ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *