በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ትራንስፎርሜሽናል ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ጥናት ሊጀመር ነው፡፡

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ትራንስፎርሜሽናል ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ጥናት ሊጀመር ነው፡፡
ጥናቱ የቢዝነስ ፖርቲፎሊዮ ክለሳ በማካሄድ ስትራቴጂን በመቅረጽ ተቋሙ የጀመረውን የሪፎርም ጉዞ ከዳር ለማድረስ የሚያስችል ነው፡፡
ጥናቱ የሚከናወነው ኤች ኤስ ቲ በተሰኘ ሃገር በቀል ኩባንያ ሲሆን የጥናት ቡድኑ በተግባር የታገዘ ድጋፍ እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡
በዛሬው እለት ከኩባንያው አመራሮች ጋር የመጀመሪያ ዙር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ውይይቱን የመሩት የግሩፑ የቦርድ አባል አቶ በዛብህ ገብረየስ ናቸው፡፡
ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች የማኔጅመንት አባላትና የማርኬቲንግ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ምክክር ግሩፑ የተሰጠውን ተልእኮ ከዳር ለማድረስ መሰናክል የሆኑ ችግሮችን በመዳሰስ በጥናቱ መፍትሄ እንደሚቀመጥለት ተመላክቷል፡፡
በጥናት ላይ ያልተመሰረቱ ፣ እዚህም እዚያም የተጀማመሩ ምርቶች ውስጥ የቆየው ተቋሙ ለውጤት እንዳልበቃ የተመላከተ ሲሆን አሁን የሚከለሰው የቢዝነስ ፖርፎሊዎ መሰል ችግሮችን ለመፍታት ያግዛል፡፡
ቴክኖሎጂም የጥናቱ አካል እንዲሆንና ግሩፑ አሁን የታጠቃቸውን የቆዩ ቴክኖሎጂዎች መፍትሄ እንዲያመላክት ተጠቁሟል፡፡
በጥናቱ ላይ የተመሰረት ስትራቴጂ የሚዘጋጅ ይሆናልም ተብሏል፡፡
ግሩፑን ለመቀየር የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን አሁን የተጀመረው ጥናት በግሩፑ ትራንስፎርሜሽናል ለውጥ ለማምጣት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *