የግሩፑ የ2014 አ.ም አፈጻጸምና የ2015 እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በተወሰኑ የምርት አይነቶች ያስገኘውን ውጤት በማስፋት ሁሉንም ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ማድረግ እንደሚጠበቅበት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የግሩፑ የ2014 አ.ም አፈጻጸምና የ2015 እቅድ ቀርቦ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው፡፡
ግሩፑ ባቀረበው ሪፖርት እንደተመላከተውም የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የሰው ሃይል መዋቅሩንና ምደባውን በመፈጸምና የኦዲት ስራውን በማከናወን የተሻለ ተግባራት ለመፈጸም መሞከሩ ተብራርቷል፡፡
ከምርታማነት አንጻር በተወሰኑ ምርቶች ላይ ውጤቶች የተመዘገቡበት አመት ቢሆንም ተቋሙ ካላው አቅም አንጻር ብዙ ቀሪ ስራዎች መኖራቸው ነው የተመላከተው፡፡
ምርታማነቱን ለማሳደግ፣ የካይዘን አሰራር ለመተግበርና የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ለማግኘት ሁሉን አቀፍ ስራዎች እየተተገበሩ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣የአቅም ማነስና መሰል ችግሮች ማጋጠማቸውም በተግዳሮትነት ተነስቷል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ በተለይ በ2015 የበጀት አመት የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግ የተለያዩ አማራጮች ተቀምጠው እየተሰራ እንደሚገኘ የተገለጸ ሲሆን የመንግስት ሚና ግን ከፍተኛ መሆኑ ነው የተጠቀሰው፡
በተለያዩ ማእቀፎች ከውጭ ኩባያዎች ጋር ለመስራት የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸው በእቅዱ ላይ የቀረበ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በተለይ በግብርና ማሽነሪ ዘርፍ፣፣በፓምፕ እና በአውቶሞቲቭ ዘርፍ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር የተሻለ ውጤቶችን ለማስመዘገብ የተጀመሩት ስራዎች በዚህ አመት ትኩረት ተሰጥቷቸው የሚከናወኑ ተግባራት መሆናቸው ተቀምጧል፡፡
የግሩፑ የቦርድ አባል አቶ አየለ ከበደ፣የግሩፑ የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ም/ል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ገብረ ማርያርም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ ማብራሪያና ምላሾችን ሰጥተዋል፡፡
ግሩፑ ከነበረበት ውስብስብ ችግር ለመላቀቅ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተው ከነዚህ ችግሮች ለመላቀቅ ጊዜ መውሰዱ አልቀረም ብለዋል፡፡
አሁን ሁሉም ተግባራት በመመሪያና በአሰራር የሚከናወኑ በመሆናቸው ዝርዝክ አሰራሮች በእጅጉ መቀነሳቸውን ገልጸዋል፡፡
ነባር ምርቶችን በስፋት ወደ ኢኮኖሚው እየቀላቀልን እንገኛን ያሉ ሲሆን ለነዚህ ምርቶች የመለዋወጫ ዕጥረት እንዳይኖር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
ከዚያም አዳዲስ ብራንዶች በጥንቃቄ በመለየት እንደሚሰራ በማስታወስ ጭምር፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በተወሰኑ የምርት አይነቶች ላይ የተገኘውን ውጤት በማስፋት በሁሉም ኢንዱስትሪዎች ላይ ማሳካት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ማኔጅመንት አባላት እና የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *