ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ባዘጋጀው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ላይ ተሳተፈ።
ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም (ሞጆ)
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና አመራሮች፣ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ፣የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ እና ፓወር ኢክዩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች አመራርና ሰራተኞች የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ከሞጆ-ሃዋሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ላይ ተሳተፉ።
በችግኝ መትከል መርሃግብሩ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን ጨምሮ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ስር የሚገኙ ዘጠኝ ተቋማት ተሳትፈዋል።
መርሃግብሩን የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ከመንግስት ልማት ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን አዘጋጅቶታል።
በእለቱም በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መሀመድ አብዶ፣የሞጆ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ፍቅሬ ጨምሮ የዘጠኙ ተቋማት አመራርና ተወካዮችን ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል።
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕም በእለቱ በተዘጋጀለት ቦታ ላይ 500 ችግኞችን አኑሯል።
ግሩፑ “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪቃል እንደሃገር የዚህ ታሪካዊ ንቅናቄ አካል በመሆን ላለፉት ሳምንታት በኢንዱስትሪዎቹ የችግኝ መትከል መርሃግብር ማካሄዱ ይታወቃል።በዛሬው እለትም የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አሻራውን አኑሯል።
በዛሬው እለት ከ 6 ሺህ በላይ የሚሆኑ ችግኞችን የመትከል ስነስርዓት ተከናውኗል።