የግሩፑ ማኔጅመንት የ2015 አ.ም አፈጻጸም እና የ2016 አ.ም እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ማኔጅመንት በግሩፑ የ2015 አ.ም አፈጻጸም ላይ እና በ2016አ.ም እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
በተጠናቀቀው የበጀት አመት በምርት፣በፋይናንስ በሪፎርም ስራዎችና በተለያዩ አፈጻጸሞች ከቀደሙት አመታት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
የግሩፑ ጥቅል አፈጻጸም 72 ነጥብ 2 በመቶ የደረሰ ሲሆን ይህም ከቀደሙት አመታት ጋር ሲነጻጸር እድገት እንዳለው በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
ይሁንና ግሩፑ ካለው እምቅ አቅም አንጻር እና የተሰጠውን ተልእኮ ከመወጣት አንጻር በርካታ ቀሪ ስራዎች መኖራቸው ተገምግሟል፡፡
እድገቱ እንዲመዘገብ የተቻለው የውስጥ አቅምን አሟጦ በመጠቀም፣ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ሃብቶችን መልሶ በመጠቀም፣የወጪ ቅነሳዎች ላይ ሰፊ ስራ በመሰራቱ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ግሩፑ በእቅዱ ልክ ውጤት እንዳያስመዘግብ እንቅፋት የሆኑት የውጪ ምንዛሪ እጥረትና የግብአት እጥረቶች በዋነኛነት የተለዩ ተግዳሮች ናቸው፡፡
እንደ ሃገር የገጠሙትን እነዚህን ተግዳሮች በመቋቋም ከዚህም በላይ ውጤት ማስመዝገብ የሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ሰፊ ምክክር ተደርጓል፡፡
በወይይቱ ወቅት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የኢንዱስትሪዎች የርስ በርስ ትስስርን በማጎልበት፣የምርምር ስራዎችን በማካሄድና ከመገጣጠም ባለፈ ማምረት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ከዚህም ባገሻገር ከተለያዩ የውጭ ኩባያዎች ጋር በጋራ ለመስራት የተጀመሩት ስራዎች ተጠናረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡
በዋነናነት አመለካከት ላይ ሰፊ ስራ መስራትና አመራርና ሰራተኛው ሃብቱን በቁጠባና ውጤት ሊያመጣ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ርብርብ ሊያደረግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በተመሳሳይ ማኔጅመንቱ በ2016 በጀት አመት እቅድ ላይ ጥልቅ ውይይት ያካሄደ ሲሆን የምርት አፈጻጸሙን በከፍተኛ ደረጃ ሊያሳድግ የሚያስችለውን ነው ተብሏል፡፡
ይህም ግሩፑንም ሆነ ሰራተኛውን ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ሊያደርገው የሚችል እቅድ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
በርካታ የውጭ ኩባንያዎች ከግሩፑ ጋር ለመስራት ፍላጎት ማሳየታቸው ታሳቢ መደረጉ ከእቅዱም በላይ ውጤት ሊመዘግብ እንደሚችል ያመላክታል ተብሏል፡፡
ከአፈጻጸሙና ከእቅዱ በተጨማሪ የውስጥ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *