ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኤሌክትሪክ ባሶችን ለማምረት የሚስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከቻይናው ሺያሚን ኪንግ ሎንግ ዩናይትድ አውቶሞቲቭ ኢንዳስትሪ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የሺያሚን ኪንግ ሎንግ ዩናይትድ አውቶቲቭ የደቡብና ምስራቅ አፍሪካ የሴልስ ዳይሬክተር ናቸው፡፡
ስምምነቱ የኤሌክትሪክና በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ባሶችን ለማምረት የሚሥችል ነው፡፡
ስምምነቱ በአጭር ጊዜ ባሶችን መገጣጠምና በመካከለኛ ጊዜ ባሶችን እስከ ማምረት የሚደርስ ነው፡፡
የቴክኖሎጂ ሽግግር በስምምነት ውስጥ የተካተተ ሲሆን በሃገር ውስጥ የሚመረቱ ግብአቶችን በማሳደግ ባሶችን በራስ አቅም እስከ ማምረት ይደረሳል፡፡

