ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የሀብት ዘርፍ የ2016 የበጀት አመት 1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ተካሄደ።
በዋና ዋና ስራዎች ላይ በኢንዱስትሪዎች ሪፖርት ቀርቧል፡፡
የሀብት ልየታ እና ምዝገባ ፣ የንብረት አጠቃቀም፣ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች የደረሱበት ደረጃ ተብራርቶ ቀርቧል፡፡በአዲሱ አደረጃጀት የሰው ሀይል ምደባ ፣የቆጠራ እና ምዝገባ ፣ የሂሳብ መዝገብን ወቅታዊ የማድረግ ስራዎችሱ የደረሰበትን ሁኔታ እና አሰራርን ከማዘመን አንፃር የተከናወኑ ስራዎች ያሉበት ደረጃ በኢንደስትሪ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሀብት ዘርፍ ቀርቦ ጥልት ውይይት ተካሂዷል።
ይህ አይነት ሪፖርት አቀራረብ የሀላፊዎችን አቅም መገንባት ላይ እና በኢንደስትሪ መካከል ልምድ ለመለዋወጥ እና ሀብትን በመጠቀም ላይ ትልቅ አበርክቶ እንዳለው በውይይቱ ተነስቷል። በውስጥ አቅም የሰራተኛዉን ኑሮ ለማሻሻል በአንዳንድ ኢንዱስትሪዎች የተሰራው አበረታች ተብሎ ተገምግሟል፡፡በመማማር እና እድገት ብቁ እና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ለማፍራት እንዲሁ በአንዳንድ ኢንዱስትሪዎች የተሰራው ስራ ትልቅ ውጤት የተገኘበት በመሆኑ በወጥነት በሁሉም ኢንደስትሪዎች ተሞክሮዎቹ እንዲቀጥሉ እና የሪፖርት አካል እንዲደረጉ መስማማት ላይ ተደርሷል።
እየተሰራ ያለው ስራ የወጪ ቅነሳ ስትራቴጂ ላይ የበለጠ በእቅድ በመምራት መሰራት እንዳለበትም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ያለውን የውጭ ምንዛሬ ችግር ለመፍታት በሚያስችል መልኩ የግብአት አማራጮች መፈለግ ላይ መስራት እንደሚገባ፣ አማራጭ ገቢ ማስገኛ ዘዴዎች ላይ መስራት እንደሚገባም እንዲሁ አቅጣጫ የተቀመጠባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡
የግዥ ስርአትን ግልፅ፣ ተአማኒ እና አዋጪ ከማድረግ አንፃር አሁንም ክፍተቶችን ለይቶ ማስቀመጥ ይገባል ተብሏል፡፡ የፋይናንስ ሪፎርም ስራዎች በእቅድ እየሄዱ ቢሆንም ቀሪ ባክሎግ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እንዲሰራ ፣ በግዥ ወቅት ከኢንዱስትሪዎቻችን ጋር ለሚኖር የትስስር ስራ ቅድሚያ እንዲሰጥ፣ ያለውን የገንዘብ እጥረት ለመቀነስ የተከማቹ ንብረቶችን ወደ ሀብት መቀየር እና የተሰብሳቢ ሂሳብ ስራ ልዪ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡የተሰጡት አቅጣጫዎች በድርጊት መርሀ ግብር ተሰርቶ እንዲቀርብ ተብሏል፡፡
የካይዘን አተገባበር ጥሩ ቢሆንም በፍጥነት በወጥነት ተሰርቶ ማጠናቀቅ ይህም በገንዘብ የሚተመን ብቻ ሳይሆን ምቹ የስራ ቦታን በመፍጠር እና በሌሎችም መስፈርቶች ተለክቶ በወጥነት የሪፖርት አካል እንዲሆንና ስራውም በድርጊት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
አሰራርን ማዘመን ጊዜ የማይሰጠው ስራ ስለሆነ የዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቅ እና ማለማመድ እንደሚገባ መድረኩን በመሩት በግሩፑ በምክትል ስራ አስፈፃሚ ሀብት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ መሰረት ደስታ አቅጣጫ ተቀምጧል።
