በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የተመራ ልዑካን ቡድን በአዲስ ማሽን መለዋወጫና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘውን የአዋሽ ፍሬን ሸራ ፋብሪካን ጎበኘ።
በቀጣይ ከክልሉ ጋር ተቀራርቦ በመስራት ፋብሪካውን ወደ ላቀ አምራችነት ለማብቃት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ፋብሪካው ትልቅ አቅም እንዳለው ጠቅሰው ለክልሉም ማኑፍክቸሪንግ እድገት ተስፋ እንዳለው ገልፀዋል።
በእለቱም የፋብሪካው እንቅስቃሴ ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የምርት ሂደቱን ለማቀላጠፍ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።
በተለይም ፋብሪካው ፍሬን ሸራ ከማምረት በተጨማሪ ከውጭ የሚገቡ ተመሳሳይ ምርቶች ጥራታቸውን የሚረጋገጥበት ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ተደርጓል።