ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከባዝራ ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ቴክኖሎጂ፣ፋይናንስና እውቀትን ወደ ሃገር ውስጥ ለማምጣት ያለመ ነው፡፡
በቀዳሚነትም ከባድ ተሽከርካሪና አውቶብሶችን፣የየኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮችንና እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶችን በሃገር ውስጥ ለማምረት ያለመ ስምምነት ነው፡፡
በቀጣይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የኢትዮ ሩሲያ ኢንዱስትሪ ዞን ለመመስረት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ነው፡፡
ስምምነቱን በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በኩል የዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ መሃመድ ጀማል የፈረሙ ሲሆን በባዝራ ግሩፕ በኩል ደግሞ ዋና ስራ አስፈጻሚው ያየህራድ አስናቀ (ዶ/ር) ፈርመዋል፡፡
