ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከማሌዥያው ሃይራክስኦይል ኩባንያ ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከማሌዥያው ሃይራክስኦይል ኩባንያ ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
የኩባንያው ተወካዮች በትንስፎርመር ዘይት ፣በማሽነሪ ዘይቶችና ሌሎች ተያያዥ ምርቶች ላይ ያላቸውን ልምድና ከግሩፑ ጋር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡
ኩባንያው በተለይ ለጥራት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ገልጿል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከተሰማራባቸው ዘርፎች ውስጥ አንዱ የትራንስፎርመር ምርት መሆኑና ለዚህም ደግሞ ጥራት ያለው የትራንስፎርመር ዘይት ወሳኝ ግብአት እንደሆነ በግሩፑ በኩል ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
ይህም ጥራት ያለውን ትራንስፎርመር ለማምረትና አስተማማኝ የሃይል አቅርቦት እንዲኖር ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተብራርቶላቸዋል፡፡
ከትራንስፎርመር ዘይት ባሻገር በሌሎች የማሽነሪ ዘይቶችና በሌሎች ተያያዥ ምርቶች ላይ በጋራ መስራት የሚቻልበት ሁኔታ በመኖሩ ፤ በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና በሃራክስኦይል ኩባንያ መካከል የጋራ መግባባት ተፈጥሯል፡፡
በደቡብ ምስራቅ ኢሲያ ታዋቂ መሆኑ የተነገረለት የሃይራክስኦይልረ ኩባንያው ሃላፊዎች የታጠቅ ትራንስፎርመር ፋብሪካን የሚጎበኙ ሲሆን በቀጣይ የትብብር ማእቀፎች ላይ ምክክር የሚደረግ ይሆናል፡፡
በግሩፑ በኩል ስብሰባውን የመሩት የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሃላፊ ጤና ግዛው(ዶ/ር) ሲሆኑ የፓወር ኢኩፕመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አንዷለም ለገሰ እና ሌሎች የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *