የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ኮማንዳንት ብርጋዴር ጀነራል ከበደ ረጋሳ ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡
ስምምቱ ሁሉን አቀፍ ትብብሮሽ ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይም በትምህርት፣ስልጠና፣በምርምር እና ልማት ስራዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በተግባር ላይ የተደገፈ የተማሪዎች ልምምድ፣የባለሙያዎች ልውውጥ፣ስልጠናና አቅም ግንባታ መስኮች ላይ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
እንደ ትምህርት ተቋምና እንደ ኢንዱስትሪ በጋራ የምርምር እና ልማት ስራዎችን ማከናወን በመግባቢያ ስምምነቱ ውስጥ የተካተተ ነው፡፡
የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችም በስምምነቱ ውስጥ ተካተዋል፡፡
በፊርማ ስምምነነቱ ወቅት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ዩኒቨርስቲው ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ለመገንባት ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን አድንቀዋል፡፡
ግሩፑም በሁሉን አቀፍ መስኮች በጋራ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ኮማንዳንት ብርጋዴር ጀነራል ከበደ ረጋሳ በበኩላቸው የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ከዳር ለማድረስ ሁሉን አቀፍ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡