ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የፍራንኮን ኢቲ አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ባለቤት ፍራንሲስኮ ቪሎኒ ናቸው፡፡
ስምምነቱ በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ ተሸከርካሪዎችን በጋራ ለማምረት የሚያስችላቸው ነው፡፡
ተቋማቱ በየራሳቸው ያካበቷቸውን እውቀት፣የገነቧቸውን የማምረቻ ፋሲሊቲዎችን እና የገበያ እድሎችን በጋራ በመጠቀም ውጤታማ ስራን ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ተቋማት የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ አጋርነትን መሰረት በማድረግ የቴክኖሎጂና የቴክኒክ ትብብሮሽን ያደርጋሉ፡፡በምርት ሎካላይዜሽን ላይም በጋራ ይሰራሉ፡፡
በስምምነቱ ወቅት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እንዳሉት በኢትዮጵያውያን የተመረቱ ተሸከርካሪዎችን ለማምረት ስምምነቱ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ዘለቄታዊ ትብብርን መሰረት አድርገን ከሰራን የሃገራችንን እና የህዝቡን ፍላጎት እናሟላለን ብለዋል፡፡
የፍራንኮን ኢቲ አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ባለቤት ፍራንሲስኮ ቪሎኒ በበኩላቸው እኛው ለእኛው ከተጋገዝን የውጭ ምርቶችን በማስቀረት በሃገር ውስጥ ማምረት እንችላለን ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያውኖች ከተባበርን እና በቁጭት ከተነሳን የተሻለ ስራን መስራት እንችላለንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡