የኢትዮ ኢነጂነሪንግ ግሩፕ ዋና መ/ቤትና በግሩፑ ስር የሚገኘው የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የጥራት ስራ አመራር ስርአት ISO 9001:2015 (Quality Management System) ትግበራ እውቅና አገኙ፡

ግሩፑ ከሃገራዊ ለውጡ በፊት በነበረው አደረጃጀት እና ተልዕኮ በርካታ የምርትና አገልግሎት ጥራት ችግር የነበረበት ፣ የደንበኛን ፍላጎት ያላማከለ ምርቶች የሚመረቱበት የልማት ድርጅት ነበር፡፡
ሃገራዊ ለውጡን ተከትሎ ወደ ሪፎርም ስራ ውስጥ የገባው ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በአዲስ አደረጃጀት እና ተልዕኮ ከተዋቀረ በኋላ ለውስጥ አሰራርና ምርታማነት ትኩረት በመስጠት ተቋማዊ የምርታማነትና የጥራት ማሻሻያ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡


በዚሁ በተከናወነው ስራም ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት በዛሬው እለት የግሩፓችን ዋና መ/ቤት እና አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች አለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአሰራር ስርዓት ሰርቲፊኬት ISO 9001:2015 (Quality Management System) ማግኘት ችለዋል፡፡
በእለቱም የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በመልእክታቸው ግሩፑን ለሀገር ልማት የሚሰራ ተቋም ለማድረግ እየተጋን እንገኛለን ያሉ ሲሆን ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶች ማምረት የሀገሪቱን የገበያ ክፍት ለመሙላት ይረዳናል ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መኣዛ አበራ ግሩፑ ላደረገው ጥረት አመሰግነው በቀጣይ በሌሎችም መስኮች በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ቀሪ ስምንቱ ኢንዱስትሪዎቻችንም በቀጣይ የሙከራ ትግበራቸውን በማጠናቀቅ ሰርቲፊኬሽኑን የሚያገኙ ይሆናል፡፡
ግሩፓችን ካሉት ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎች አንዱ ኢንዱስትሪ ማለትም የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ብቻ ቀድሞ የISO 9001:2015 (Quality Management System) የአሰራር ስርዓት በመተግበሩና ሰርቲፋኬቱን ማግኘቱ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *