የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሃላፊ ሆነው ለተመደቡት አቶ ሳሙኤል ሃላላ የአቀባበል ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስራ አመራር ቦርድ በቅርቡ የሰጠውን ምደባ ተከትሎ ነው ፣የግሩፑ ማኔጅመንት የአቀባበል ፕሮግራም ያዘጋጀው፡፡
በስነ ስርአቱ ላይ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልእክታቸውም ሁሉም የስራ ሃላፊዎች የተለመደውን የስራ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በስራ አመራር ቦርድ ውስጥ መቆየታቸውንም በመጥቀስ ግሩፑን ለተሻለ ውጤት ለማብቃት ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል፡፡
አዲስ የተመደቡት የግሩፑ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ሃላላ በበኩላቸው የግሩፑ ማኔጅመንት ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡
በተለያዩ ተቋማት በመስራት ያካበቱትን እውቀትና ልምድ ለግሩፑ ውጤታማነት ለማበርከት ብርቱ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *