ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በተያዘው በጀት አመት ባለፉት ስድስት ወራት ትርፋማነቱን ማስቀጠሉ የሚበረታታ መሆኑ ተገለፀ።

ግሩፑ በዛሬው እለት ለገንዘብ ሚኒስቴር እና ለመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የ2016 ዓ.ም የ6 ወር አጠቃላይ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርቦ ግብረ መልስ ተሰቶበታል።


በሪፖርቱ ከምርት ፣ከገቢ አፈፃፀም፣ ከሽያጭ አፈፃፀም፣ ከተሰብሳቢ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ቅልጥፍና ፣አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎች፣የጥራት ስራ አመራር ፣የተጀመሩ ፕሮጀክቶች፣ የካይዘን ትግበራ እንዲሁም የማህበራዊ ሀላፊነት ተግባሮች በዝርዝር ቀርበዋል።
በውይይቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ግሩፑ ትርፋማነቱን ማስቀጠሉ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


ሆኖም ግን ከተያዘው አመታዊ እቅድ አንፃር ትርፉ አነስተኛ እንደሆነ አንስተዋል።
በተሰብሳቢና በዕዳ ስረዛ ለሚያጋጥሙ ጉዳዮች ከተቋሙ ጎን እንደሚቆሙ የገለጹ ሲሆን የማምረት አቅምን በማሳደግ የወጭ ቅነሳ ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በበጀት አመቱ የተያዘው እቅድ ብዙ ቢሆንም ከነበሩት ተግዳሮቶች አንፃር የተቋሙን ትርፍ ማስቀጠል እንደተቻለ አብራርተዋል።


የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣የማሽነሪዎች ብልሽት፣ የሀይል መቆራረጥና የፋይናንስ እጥረት ለተመዘገበው ትርፍ ማነስ እንደ ተግዳሮት የተነሱ ቢሆንም ኪሳራ ላይ የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት መመለሳቸው የሚበረታታ ውጤት እንደሆነ ተገልጿል።
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በግሩፑ ውስጥ ያሉትን ጥንካሬዎችና ክፍተቶችን የሚያሳይ ግብረ መልስም በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *