ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና ኢሊንክ የተሰኘው የቻይና ኩባንያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የኢሊንክ ኩባንያ ሲኒየር ቢዝነስ ማናጀር ዋንግ ዪ ፈርመውታል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና ኢሊንክ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ለመገጣጠምና ለማምረት ፣በሂደትም በሀገር ውስጥ ለማምረት ፣በምርምርና ልማት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ስምምነት ተፈራርመዋል ፡፡
ስምምነቱ መሰረት ካሽ ሪጅስተር ማሽን፣ ስማርት ቴሌቭዥን ፣ ታብሌት ፣ዘመናዊ የመብራትና የውሃ ቆጣሪዎች በጋራ ለማምረት ያስችላል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *