በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የምርምርና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዘርፍ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

ግንቦት 21/2016 ዓ.ም (ኢኢግ) የምርምርና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዘርፍ በስሩ ካሉት መምሪያዎች ከተውጣጡ አመራርና ባለሙያዎች ጋር የትውውቅና ውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የምርምርና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዘርፍ ኃላፊ ጤና ግዛው (ዶ/ር ) ዘርፉ ግሩፑ ይዞት የተነሳውን ተልዕኮ ለማሳካት ወሳኝ የተቋሙ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤የተቋሙንና የሃገሪቱን ራዕይ ከግብ ለማድረስ አዳዲስ ሃሳቦችን በማመንጨት ወደ ገበያ መቀየር ይገባል ብለዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ከባለሙያ ጀምሮ እስከ አመራር ያለው አካል የሚጠበቅበትን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡
በእለቱም ከግብይትና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት፣ ከምርምር ስርፀትና ፕሮጀክት ማኔጅመንት መምሪያና በየክፍሉ ካሉ አመራሮች በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በበጀት አመቱ በስራ ሂደት ውስጥ የታዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶችና ጥንካሬዎች ተለይተው የቀረቡ ሲሆን ችግሮችን ለመፍታት በሚቻልባቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተዋል፡፡
ከምርምርና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዘርፍ ተልዕኮ እንፃር የሚፈለገው ውጤት እንዲታይ በመምሪያዎቹ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ የግንኙነት ማዕቀፍ በመፍጠር የግሩፑን ተልዕኮ ወደ ተግባር ማሸጋገር እንደሚገባ ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *