ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከፎቶን ኩባንያ ጋር በጋራ ተሸከርካሪዎችን ማምረት የሚያስችለውን ውይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ፣ የፎቶን ኩባንያ ፕሬዝዳንት ፉ ጁን፣እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በቀረበው ገለጻ ፉቶን ቀላል፣መካከለኛና ከባድ ተሽከርካሪዎችን፣ቫን፣ፒክ አፕ፣ኤስ.ዩ.ቪ፣ባሶችንና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን በማምረት ለአለም ገበያ እያቀረበ ነው፡፡
ፎቶን ለአለም ገበያ 11 ሚሊየን ተሽከርካሪዎችን ያቀረበና የካርበን ልቀት መጠናቸው ዜሮ የሆኑ፤ በአውቶሜትድ የተመረቱ ተሸከርካሪዎችን በማምረት ላይ ይገኛል፡፡
በውይይቱ እንደተመላከተው ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና ፎቶን በጆይንት ቬንቸር በተለይም ባሶችና ፒክ አፖች ላይ አተኩረው በጋራ ሊያመርቱ ይችላሉ፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካ ገበያ ያልተነካ በመሆኑ በጋራ ገበያውን ማዳረስ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
በተለይም የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ላይ በመስራት ከመንግስት ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ ልማት ማምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
የፎቶን ኩባንያ ፕሬዝዳንት ፉ ጁን በበኩላቸው ከግሩፑ ጋር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል፡፡
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪን በማዘመን ምርቶቹ የሚመረቱበት መንገድን ማመቻቸት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ዝርዝር የስምምነት ሰነዶችን በጋራ በማዘጋጀትና በመፈራረም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመግባት ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *