ኢኢግ (ጥር 13/2017 ዓ.ም) የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ አመት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
ግሩፑ አፈጻጻሙን ለስራ አመራር ቦርድ አባላት አቅርቦ ነው ውይይቱ የተካሄደው፡፡
በቀረበው ሪፖርት መሰረት የግማሽ ዓመቱ ጥቅል የምርት አፈጻጸም ከአምናው ጋር ሲነጻጸር መሻሻል የታየበት ነው፡፡ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት በ31.6% መጨመር አሳይቷል፡፡
በበጀት አመቱ ግማሽ አመት ግሩፑ ከታክስ በፊት 99.41 ሚሊየን ብር ለማትረፍ አቅዶ 126.05 ሚሊየን ብር ማትረፍ ችሏል፡፡
ግሩፑ ካለው ተጨባጭ የማምረት አቅም 27 በመቶውን መጠቀም ችሏል፡፡
በበጀት ዓመቱ 186.14 ሚሊየን ዶላር ከውጭ ለሚገቡ ግብዓቶች የሚያስፈልግ ቢሆንም በግማሽ ዓመቱ 8.842 ሚሊየን ዶላር ብቻ ተገኝቶ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር ተደርጓል፡፡ ይህም ከዕቅድ አንጻር 4.75% ብቻ ነው፡፡
ይህም ተቋሙ የአቅሙን ያክል እንዳያመርት አድርጎታል፡፡
ሆኖም ከግል ባንኮች በተገኘው ውስን የውጭ ምንዛሪ እና ከፋይናንሰሮች በተገኘ የውጭ ምንዛሪ ኢንዱስትሪዎች ግብአት በማስገባት ላይ ይገኛሉ፡፡
የግሩፑ ኢንዱስትሪዎች የአሰራር ጥራት ማረጋገጫ(ISO 9001:2015) ለማግኘት እየተሰራ ሲሆን በበጀት አመቱ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ማግኘት ችሏል፡፡የምርት ጥራት ማረጋገጫ ለማግኘትም ተከታታይ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡የስቶር ካይዘን ስራ ላይም አመርቂ ስራዎችን ተከናውኗል፡፡
ግሩፑ የሰው ሃይሉን አቅም ለመገንባት የስልጠና ማእከልን በተደራጀ መልኩ ስራ አስጀምሯል፡፡
የፋይናንስ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በማቋቋም በውጭ ኦዲት ለማስደረግ እየተሰራ ያለው ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡በተቋሙ የERP አሰራር ለመዘርጋት እየተሰራ የሚገኘው ስራም እየተፋጠነ ነው ተብሏል፡፡
ግሩፑ በሁሉም መስክ ያስመዘገበው ውጤት አበረታች ቢሆንም የግብዓት እጥረት አሁንም ችግር ሆኗል ተብሏል፡፡ይህንን በፋይናንስ እጥረት እየተከሰተ ያለውን የግብአት እጥረት ለመፍታት የተለያዩ አማራጮች ተፈልገው እንዲሰራ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል፡፡
ቦርዱ በቀጣይ ቢተገበሩ ያላቸውንም አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡በተለይም የሰው ሃይሉን ውጤታማናትና አገልጋይነት ላይ በትኩረት እንዲሰራበት ብሏል፡፡ሰራተኞችን አነቃቅቶ እና አብቅቶ ለማሰማራት ጥረት ቢደረግበት የተባለ ሲሆን የፋይናንስ፣የስጋት አስተዳደር ስራዎችን ጤናማነት እያረጋገጡ መሄድ ይገባልም ብሏል፡፡







