ኢኢግ (የካቲት 03/ 2017 ዓ.ም) በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ   ኢንዱስትሪ ዘመናዊ  የዋይ. ቲ. ኦ ትራክተሮችን ለመገጣጠም  የሚያችለውን ግብአት አስገባ፡፡

ኢኢግ (የካቲት 03/ 2017 ዓ.ም) በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ   ኢንዱስትሪ ዘመናዊ  የዋይ. ቲ. ኦ ትራክተሮችን ለመገጣጠም  የሚያችለውን ግብአት አስገባ፡፡
ትራክተሮቹ በኤስ ኬ ዲ የገቡ ሲሆን 118 ትራክተሮችን ለማምረት ያችላል፡፡
ከ60 እስከ 95 የፈረስ ጉልበት ያላቸው ትራክተሮችን በማምረት ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ የሚያስችል ነው፡፡
በተጨማሪም ለሁሉም ትራክተሮች ማረሻና መከስከሻ ለመግጠም የሚያስችልም ግብአት አብሮ ገብቷል፡፡
ከዚሁ ከዋይ ቲ ኦ ኩባንያ ተጨማሪ 300 ትራክተሮችን ለመገጣጠም የሚያችል ግብአት ለማስገባት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አካል የሆነው አዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በ1976 የተመሰረተ አንጋፋ ኢንዱስትሪ ሲሆን የሃገሪቱን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *