የካቲት 18/2017 ዓ.ም (ኢ.ኢ.ግ) ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ትርፋማነቱን እያስቀጠለ መምጣቱ የሚበረታታ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ገለጸ፡፡የግሩፑ የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል፡፡

ግሩፑ ባለፉት ሶስት አመታት ወደ ትርፍ መሸጋገሩ የሚበረታታ መሆኑና አሁንም ትርፉን ለማሳደግ የተለያዩ ግብአቶችን ከውጭ እያስገባ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
ግብአቶችን በሚፈለገው ደረጃ ለማስገባት ያለውን የፋይናንስ እጥረት ለመፍታት ከግል ባንኮችና ከተለያዩ የፋይናንስ ምንጮች ጋር በጥምረት እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
የኢትዮያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፑ የጀመረውን ትርፋማነት ለማስቀጠል እያሄደበት ያለው መንገድ የሚበረታታ ነው ብሏል፡፡
የገቢ እድገት እያስመዘገበ መሆኑ ደግሞ ለተቋሙ ወሳኝነት እንዳለው ተብራርቷል፡፡
ግሩፑ በተለያዩ ዘርፎች ለሃገር ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ ኢንዱስትሪዎችን ያቀፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዋጋ፣ በጥራትና በጊዜ ማቅረብ ላይ የበለጠ ተወዳዳሪ ለመሆን መስራት እንደሚገባ ተነስቷል፡፡
ኦፕሬሽናል አፈጻጸምን ማሳደግ፣ የሰው ሃይል አጠቃቀምን ማጎልበት፣ኢንቨንተሪ ማስተካከል፣ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የምርት ስብጥሮች ልየታ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ነው የተባለው፡፡
ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በጆይንት ቬንቸር ተጣምሮ የሚሰራባቸውን መንገዶች ማማተርና ተጨማሪ አቅሞችን መፍጠር ይገባዋል ተብሏል፡፡
በግሩፑ እየተዘጋጀ በሚገኘው የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ የግሩፑን ስትራቴጂ በደንብ መፈተሸ እንደሚያስፈልግ ተብራርቷል፡፡

ከውይይቱ በተጓዳኝ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪና ዝቋላ ስቲል ሮሊንግን የሆልዲንጉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬና የሆልዲንግ አመራሮች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ መቀላቀሉ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *