የካቲት 25/2017 (ኢኢግ) በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በቻርጅ የሚሰራ ስኩተር ማምረት ጀመረ።

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የቻይናው ጂአክሲን  ኩባንያ ጀነራል ማናጀር ሚስተር ሮቢን ጅን የስኩተር ምርት ለማምረት የሚያስችለውን ስምምነት ፈርመውታል፡፡
ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከሚያመርታቸው ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ በቻርጅ የሚሰሩ የስኩተር ምርት በዛሬው ዕለት ጀምሯል።
በመደበኛ ቻርጅ የሚሰሩት ስኩተሮች በአንድ ቻርጅ እስከ 30 ኪ.ሜ የሚጓዙ፤ የፓርኪንግ ቦታ የማይፈልጉ እና ክብደታቸው 15 ኪ.ግ ብቻ በመሆኑ በቀላሉ ወደ ቢሮና ቤት ለመግባት የሚችሉ ናቸው፡፡
ከአከባቢ ብክለት ነጻ የሆኑ፤ የትራንስፖርት ችግርን ለማቃለል የሚጠቅሙ ዘመናዊ የትራንስፖርት አማራጮች ሆነው የመጡት ምርቶቹ ተጣጣፊና በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡
በስምምነቱ ወቅት አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ ሀገራችን ላይ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ላይ አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት  እንደሚሰጡ ጠቅሰው በቅርብ ቀንም ወደ ገበያ እንደሚወጡ ገልፀዋል።
የጂአክሲን  ኩባንያ ጀነራል ማናጀር ሚስተር ሮቢን ጅን በበኩላቸው በበኩላቸው ስኩተሮቹ ደህንነታቸው የተጠበቁና በሰአት ከ20- 30 ኪ/ሜ የሚጓዙ ሲሆን አዲስ አበባ ላይ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ የሚቀንስ መሆኑን ተናግረዋል።  ምርቶቹ  በተመለከተ የአጠቃቀም ማብራሪያ ተሰጥቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *