በስምምነቱ መሰረት ሳኒ ኢንተርናሽናል ኩባንያ ዊል ሎደር እና ቼይን ኤክስካቫተር በኤስ ኬ ዲ የሚያቀርብ ሲሆን ሃንግዙ ትሩማክስ ኩባንያ ደግሞ ባቺንግ ፕላንት እና ክሬሼር ፕላንቶችን በኤስ ኬ ዲ ለማቅረብ ነው፡፡
ስምምነቱ በግሩፑ ስር የሚገኘውን የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለሚያቀርባቸው የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ፕላንቶች ግብአት የሚሆኑ ናቸው፡፡
ስምምነቱ ከኤስ ኬ ዲ ባለፈ በቀጣይ ኢንዱስትሪው በራስ አቅም ሎካላይዝ ለማደረግ ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ነው፡፡
ማሽነሪዎቹ እና ፕላንቶች በሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ለተሰማሩ የግል እና የመንግስት አልሚዎች የሚቀርቡ ናቸው፡፡
ስምምነቱ በግሩፑ ስር የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እና የተጣለባቸውን ተልእኮ በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል ነው፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክብሩ መንግስቴ ሲሆኑ ፤ከሳኒ ኢንተርናሽናል ኩባንያ በኩል የምስራቅ አፍሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ዊልሰን ዩ እና ከሃንግዙ ትሩማክስ ኩባንያ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ቼን ናቸው፡፡
ግሩፑን በመወከል የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሸጋው ሙሉጌታ እና የግሩፑ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የኢንዱስትሪው የማናጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን የሁለቱ ኩባያዎች ተወካዮችም ተገኝተዋል፡፡







