ሃምሌ 16/2018 (ኢኢግ) የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የ2018 ዓ.ም አመታዊ አፈጻጸም የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ፡፡

ሃምሌ 16/2018 (ኢኢግ) የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የ2018 ዓ.ም አመታዊ አፈጻጸም የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ፡፡
በመድረኩ በዋና መ/ቤት የሚገኙ የስራ ክፍሎችና ኢንዱስትሪዎች አፈጻጸማቸውን፣ ያጋጠሟቸውን ችግሮች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫቸውን አቅረበዋል፡፡

የግሩፑ አጠቃላይ አፈጻጸም ማጠቃላያም በፕላንና ፕሮግራም የቀረበ ሲሆን በ2018 አ.ም በምርት፣ በሽያጭ ፣ በገቢ እና በትርፍ ከፍተኛ እድገት መመዝገቡ ተገልጿል፡፡
ለዚህ ደግሞ ማናጅመንቱ እና ሰራተኛው ያደረገው ርብርብ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ግሩፑ በሪፎርም ስራዎችም የዴሉኬዌንት ሂሳብ በማወራረድ፤ የቆዩ የህግ ጉዳዮችን በድርድር መጨረስን ጨምሮ የውስጥ ኦዲት ግኝቶችን ለማስተካከል የተሰሩ ስራዎች አበረታች ተብለው ተገምግመዋል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሸጋው ሙሉጌታ(ኢ/ር) ግሩፑ በለውጥ ላይ እንደሚገኝ አብራርተው ይህንን ለውጥ በከፍተኛ ደረጃ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
የተገኘው ውጤት የሚያበረታታ መሆኑን አስረድተው ኢንዱስትሪዎቹ ካላቸው እምቅ አቅም አንጻር ብዙ ቀሪ ስራዎች አሉ ብለዋል፡፡

ይህንንም ለማሳካት በ2019 ዓ.ም ምርትን በ55 ፐርሰንት ለማሳደግ እና የአቅም አጠቃቀምን አሁን ከደረሰበት በአርባ ሁለት ከመቶ ለማሳደግ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
ለዚህም አዳዲሰ ስልቶችን ቀይሶ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ከዕቅዱ ጋር የሚሄዱ አዳዲስ ትዕዛዞችን መቀበል፤ስትራቴጂክ ሶርሲንግ በማመቻቸት ያልተቆራረጠ ግብአት ማመቻቸት፤የማሽን ክትትልና ጥገና ክፍልን ማጠናከር በትኩረት ሊሰራባቸው ይገባል፡፡
የምርት እቅድና ክትትል እና የኢንጂነሪንግ ስራዎችን ማጠናከር፤የደንበኛ እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ምርቶችን በፍጥነት፣ በጥራት እና በተወዳዳሪ ዋጋ ማቅረብ ይገባልም የተባለ ሲሆን ሌሎች ስልቶችም ቀርበው አቅጣጫ ተቀምጦባቸዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያም በሽያጭና ትርፍ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎች ተለይተው እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *