ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም( ኢኢግ) የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የስራ አመራር ቦርድ የግሩፑን የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄድ፡፡
ቦርዱ ግሩፑ በበጀት አመቱ በምርት፣ በሽያጭ በገቢ እና በትርፍ ያከናወናቸው ስራዎች እና የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን ገምግሟል፡፡
አፈጻጸሙ ከእቅድም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅትም ዕድገት ማሳየቱ የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ በቀጣዩ በጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ሊመዘገብ ይገባል ብሏል፡፡
የኦዲትና የስጋት አፈጻጸም እና እቅድም የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል የበለጠ ስኬታማ ተቋም ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
በቀጣይ በጀት አመት አመራሩና ሰራተኛው የበለጠ ቁርጠኛ በመሆን ግሩፑ የተሠጠውን ተልእኮ በይበልጥ እንዲወጣ ማድረግ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡






















