በኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦፕሬሽን ዘርፍ የተሾሙት ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ በኢንዱስትሪዎች የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

ሃላፊው የአዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኢንዱሰትሪንና የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስን ሲጎበኙ የኢንዱሰትሪዎች አመራሮች ስለተቋማቱ የስራ አንቅስቃሴ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ም/ዋ/ስራ አስፈፃሚ ለኦፕሬሽናል ዘርፍ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸው ኢንዱስትሪዎቻቸን የገበያ ፍላጎትን ባማከለና ተወዳዳሪነትን የተከተለ ስራ መሰራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
 
በተመረጡ የምርትና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ በጥናት የተደገፈና ጥናቱን መነሻያደረጉ ስራዎችን መስራት በምርት ጥራት ዋጋና የአቅርቦት ፍጥነትን መከተል ተወዳዳሪነት ሊያሳድጉና የደንበኞችን ማርካት አንዱና ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባው በጉብኝቱ ወቅት ተነሱ ሃሳቦች ናቸው፡፡
ለዚህም የምርት ጥራትና ተወዳዳሪነት ተግባራዊ ለማድረግ የየተቋማቱን የውስጥ አሰራር በማሻሻልና በተመረጡ ምርቶች ላይ በአትኩሮት መስራት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *