የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ሰራተኞች በሰንዳፋ ከተማ አከባቢ የሚገኙ የሰንዳፋ አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ጅማ ሰንበቴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ አይነት አገር በቀል ዛፎችን ተክለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የኢንዱስትሪው ስራ አስኪያጅ፤የተለያዩ ስራ ክፍል ሰራተኞችና የሰንዳፋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሳታፊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
በዚህ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የተለያዩ ዓይነት ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ኢንዱስትሪው በቀጣይነት እንክብካቤ እንደሚያደርግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሰንዳፋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደገፋ ፀጋዬ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር በዚህ የአረንጓዴ አሻራ ስራ መሳተፋቸውን አስመልክቶ በከተማ አስተዳደሩ ስም ለኢንዱሰትሪው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡